የሺ ሰዉ ግምት ቲያትር ሙሉዓለም የባህል ማዕከል!

አማራ ክልል የቲያትር እና የተለያዩ ጥበባት የመድረክ ስራዎች ከተመልካች እጦት ወደ አገግሞ አዳራሽ እስከመሙላት ሁኔታዎች ተጀምረዋል ።

የሺ ሰዉ ግምት ቲያትር ሙሉዓለም የባህል ማዕከል!

አማራ ክልል የቲያትር እና የተለያዩ ጥበባት የመድረክ ስራዎች ከተመልካች እጦት ወደ አገግሞ አዳራሽ እስከመሙላት ሁኔታዎች ተጀምረዋል ።

ሳቅ እንደምንጭ ዉሃ እየፈለቀ በአብሮነት ጥግ የሚደሰቱበት የሺ ሰው ግምት አዲስ ኮሜዲ ቲያትር ይዘን መተናል ።

በአንጋፋው የአብክመ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ትናንት ቅዳሜ 28/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ። የሺ ሰዉ ግምት ቲያትር ተመርቆ ተከፈቷል።

ተዋናዮች ተውኔቱን ተውነውታል ሳይሆን ህይወታቸውን ኑረውታል ያስብላል፤ ከትዕይት ትዕይንት ለተመልካች አዲስ የሳቅ ምንጭ ፡ ደስታን የሚፈጥር ኮሜዲ ቲያትር ነዉ።

የቲያትር ጥበብ በህብረተሰብ ዉስጥ እሴቶችን መጠበቅ እና መተረክ ፤ ባህላዊ ማንነትን ፣ የሞራል እሴቱን እና የጋራ ታሪክን በማንፀባረቅ ለህብረተሰቡ እንደ መስታወት ሆኖ ይሰራል።

በገፀ-ባህሪያት እና ንግግሮች ወጎችን፣ ስነ-ምግባርን እና ጥበብን ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው ያስተላልፋል። ተውኔቶች እንደ ፍትህ፣ ርህራሄ፣ ታማኝነት፣ ወይም ድፍረትና ፍርሃት በተጨባጭ በሰዎች ትግል ውስጥ ረቂቅ እሴቶችን ያሳያሉ ።

ወደ ሌሎች ህይወት ውስጥ በመግባት፣ የተለያየ ኩነትን ትግል እና እምነት ለሰዎች ጥልቅ ስሜትን ያዳብራል ። አስፈላጊ የሆኑትን ማህበራዊ ስምምነትን እና መቻቻልን ለመፍጠር ቁልፍ መሳሪያ ነው።

ሰዎች ታሪካቸውን እንዲናገሩ፣ ህመማቸውን እንዲገነዘቡ እና የጋራ የወደፊትን ጊዜ እንዲያስቡ ያስችላቸዋል፣ ይህም ለሀገር አንድነት እና መልሶ ግንባታ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ዘወትር ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ በሙሉ ዓለም የባህል ማዕከል ይታያል ።

ይምጡ ይመልከቱ! ቲያትርን ያድንቁ ! ያበረታቱ !

የሺ ሰው ግምት !

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top