የሙሉዓለም የባህል ማዕከል በደጃ አዝማች ኃይሉ ከበደ ዙሪያ የጥናትና ምርምር የፓናል ውይይት እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አካሄደ
መርሀግብሩ የማዕከሉ ሠራተኞች እና የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ማህበራት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም እንደገለፁት በተለይ በደጅ አዝማች ኋይሉ ከበደ የህይወት ታሪክና አርበኝነት የቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ እጅግ አስተማሪና ትውፊቱንና ባህሉን እንዲሁም ታሪኩን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያስተላልፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል። የማዕከሉ የጥናት ባለሙያ አርቲስት ንብረት ያለው በበኩሉ የጀግኖቻችን ታሪክ ማጥናትና ለቴአትርና ለሙዚቃ ግብዓትነት ከመጠቀም ባሻገር ትውልዱን በመረጃ ላይ ተመስርቶ በኪነ-ጥበብ እያዝናኑ ለማስተማር ጥናትና ምርምር ለትውፊታዊ ስራዎች የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም መሠል ጥናቶችን ለማጥናት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል። በቀረበው ጥናታዊ ፁህፍም የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው በአጥኝው ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይም የተነሱ ሀሳቦችን በማካተት ወደ ቴአትር ድርሰት እንደሚቀየር በአፅኖት ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪም የማዕከሉ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በማዕከሉ የዕቅድ በጀት ግምገማ እና ክትትል ቡድን መሪ በሆኑት አቶ ሀይማኖት ደሳለኝ ቀርቦ ውይይት ከተካሄደ በኋላ በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች የሚመለከታቸው የማዕከሉ የተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች፣የዕቅድ ቡድን መሪ እና የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ምላሽና ማጠቃለያ ከተሰጠ በኋላ በ2017 በጀት ዓመት የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራትን የሚያሳየውን የፎቶግራፍ ኤግዚብሺን በመጎብኘት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።
ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነው!!
ሰኔ 2017 ዓ.ም
ሙሉዓለም የባህል ማዕከል
#ዲጅታል ሚዲያ ገፆቻችንን ይቀላቀሉ።



YouTube: https://www.youtube.com/@mulualemculturalcenter/videos
Telegram: https://t.me/mulualemculturalcenter
Face Book: https://www.facebook.com/mulualem.culture.5?mibextid=ZbWKwL
Instagram: https://www.instagram.com/mulualemculturalcenter/
Tiktok : tiktok.com/@mulualemculturalcenter